ዝምታ
ምን ቢቀባጥሩ
ድምፅም ዘለግ ቢል
ጆሮ ቢያደነቁር
ምላስ ቢንቀለቀል
ማን አለ እንደ ዝም
ጮሆ የሚያናግር
ዘላለም ሽታሁን
ከ ሲያትል
ዘላለም ሽታሁን
|
ግማቱ እስኪለቀዉ
በማታዉቁት ነገር
በማያገባችሁ
በሰዉ ግል ጉዳይ
ጥልቅ እያላችሁ
በሀሜት ሞራልን
እያላሸቃችሁ
እስካሁን ብቆይም
እንዲሁ አብሬያችሁ
አሁን ግን ቀረናኝ
ሸተተኝ ወሬያችሁ
እናም ስለገማኝ
ይህ አጉል ልምዳችሁ
ሽታዉ ስለገፋኝ
ዛሬ እንዳልቀርባችሁ
ግማቱ እስቂለቀዉ
የወሬ ሱሳችሁ
ይብቃን እንለያይ
ተዉኝ ስተዋችሁ
ፈረንጂኛ አይደለም
የማናግራችሁ
ጥሩ አማርኛ ነዉ
የምለዉ ይግባችሁ
እሸቱ ደምሴ
ሐምሌ 7 1993
For constructive comments, the auther can be reached at admin@ethionation.com |
ንገረኝ መቶ ብር
እኔ ስጠፋብህ
ፈልግህ ምትመጣዉ
ለ እኔ ምትመቸኝ
እሸ ነህ ምትለዉ
በሳጥኑ ቆልፎ
ከሚያፍነኝ ሌላዉ
ታሽጌ ከምኖር
ዉጭዉን ሳላየዉ
አንተ ስትይዘኝ ነዉ
ነፃ የምሆነዉ
ከሳጥን ወጥቼ
በኩራት ምዞረዉ
ቡና ቤት ምሽት ቤት
ገብቼ ምዝናናዉ
አፈሪካና ሬጌ
ራፕ ምጨፍረዉ
እሸ ልሙትልህ
ካነተ ጋር ስሆን ነዉ
ካንተ ከምለያይ
ሞቴን ነዉ ምመርጠዉ
እንዲህ አንዳላልከኝ
ዛሬ ጠፋህ ምነዉ
ምን ነገር መጣና
ቃልክን የረሳኸዉ
ጭራሽ ስፈልግህ
መደበቅህ ምነዉ
ወይስ ሠዉ አገኘህ
ከእኔ ምታበልጠዉ?
ንገረኝ መቶ ብር
ሚስጠሩን ልወቀዉ
ንገረኝ መቶ ብር
ናፍቄህልሞትነዉ
እሸቱ ደምሴ
For constructive comments, the auther can be reached at admin@ethionation.com |
መጭዉን ለማየት
የተዛባን ሃሳብ
በምክር ኮርኩሞ
ወልጋዳ አቋምን
በትእግስት ገምግሞ
ቁንፅል አላማንም
በፅናት አክሞ
መገኘት ይበጃል
ራስን አርሞ
መጭዉን ለማየት
ከዛሬ ላይ ቆሞ
እሸቱ ደምሴ
21/12/1992
For constructive comments, the auther can be reached at admin@ethionation.com |
መቸገር ጥሩ ነዉ
ሀቀኛ አጋርን
ወዳጅን ለማወቅ
ቀን ሲያጋድል አይቶ
ሚረዳና ሚርቅ
የትኛዉ እንደሆን
ሲከፋህ ሚጨነቅ
ማንስ እነደሆነ
በዉድቀትህ ሚስቅ
መቸገር ጥሩ ነዉ
ጓደኛን ለማወቅ
ለሚመጣዉ ጊዜ
ቀድሞ ለመጠንቀቅ
እሸቱ ደምሴ
For constructive comments, the auther can be reached at admin@ethionation.com
03/07/1993 |
ማየቱ ይሻላል
ዉሉ የጠፋዉን
የሃሳብ ቋጠሮ
ከመፍታቱ ይልቅ
በአእምሮ ቀብሮ
ከዉስጥ ከመብሰልሰል
አንገት አቀርቅሮ
እኛ ማን እንደሆን
አሁንና ድሮ
ማየቱ ይሻላል
ዓይንን ከልብ ቀብሮ
እሸቱ ደምሴ
21/12/92
For constructive comments, the auther can be reached at admin@ethionation.com |
ተነስ ተንቀሳቀስ
ተነስ ተንቀሳቀስ
የእስካሁኑ ይብቃህ
ክቡር ነፃነትህን
አትስጥ አሳልፈህ
ፍፁም አታመንታ
አድምጠኝ ስነግርህ
ይበቃሀል እና
የእስካሁኑ እስርህ
ቀንበሩን ስበረዉ
ቀርቧል ነፃነትህ
ሁሉም እንደሚለዉ
እንዳልሆንክ መናኛ
ጊዜዉ ደርሶልሃል
ያንተ መፈተኛ
አሁን ወጥቶልሃል
የጠፋዉ ብርሃንህ
ነፃ የመዉጫህን
መንገዱን ሊያሳይህ
ስለዚህ ተነሳ
ምን ትጠብቃለህ
ፈርቶ በማመንታት
እድሉ አያምልጥህ
ይህ አይደለምና
ላንተ ሚሆን ጎራ
ዘራፍ ወንዱ ብለህ
ተነስ እና አቅራራ
ያንተ ጊዜ መጧል
ድፈር እንጅ አትፍራ
አዎ አስተዉለዉ
መዉጣቱን ብርሃን
በዚህ አጋጣሚ
አዉጅ ነፃነትህን
የወጣልህ ፀሃይ
ገብቶ ሳይሸፈን
ተነስ ተንቀሳቀስ
ስበረዉ ቀንበርክን
እሸቱ ደምሴ
10/16/1992
The writter can be reached at admin@ethionation.com |
ሳንቋጥር ስንቃችን
የ ጊዜዉን ዑደት
እንደቀልድቸልብለን
ሰዓቱን ጠብቆ
ጨለማ መምጣቱን
አዉቀን እንደማናዉቅ
ዘንግተን ረስተን
እንደ ጓያ ነቃይ
እያልን የፊትፊቱን
የሚገኝ ይመስል
ሁልጊዜ ብርሀን
ለ ደቂቃ እንኩዋን
ሳንወስድ ጥንቃቄን
ጨለማዉ ለንጋት
እስኪለቅ ቦታዉን
ከጠዋት መድረሻ
ሻማ ጧፍ ሳይኖረን
ዝግጅት ሳናደርግ
ቀኑን አንቀላፍተን
ምን ዋጋ አለዉ መሮጥ
ሲመሽ አየባነን
በብርሀን ጊዜ
ሳንቋጥር ስንቃችን
ምን ሊፈጥርልን ነዉ
ሲመሽ መጮሀችን
እሸቱ ደምሴ
10/11/93 ኢ.አ
The writter can be reached at admin@ethionation.com |
ተወዉ አትጨነቅ
ተወዉ አተጨነቅ አትሙት በሃሳብ
ላይቻል ቆዝሞ ችግርን መገደብ
የምተፈልገዉ የነገሮች ኡደት
ቢዘገይብህም ወይ ቢሄድ በፍጥነት
ለዉጥን አያመጣም ያንተ መበሳጨት
ስለዚህ አትዘን በሚገጥምህ ነገር
ራስክን አትጉዳ ፍፁም አትሸበር
አይቀርም ማለፉ ማንኛዉም ችግር
ይሄ ነዉ ወዳጄ ላነተ ያለኝ ምክር
ይህም ያልፋል ብለህ በደስታ ዘምር
ሀዘንን ረግጠህ በመዝናናት ፎክር
ወፎችንም አድርግ ላንተ ምሳሌ
ሳያዝኑ በደስታ ሲዘምሩ ሁሌ
ታዲያ ብትበልጥ እንጅ ከወፎች አታንስም
የህንም ተረድተህ አትዘን አትቆዝም
ማንኛዉምችግርመለወጡአይቀርም
እሸቱ ደምሴ
The writter can be reached at admin@ethionation.com |
የዛሬ ሰዉ
እስክትገባ ፀሃይ ወጥታ
በጨረቃ ተተክታ
እየቁዋጠርን ስንፈታ
እዚህ ደረስን በዝግታ
ያለፈዉን እያወደስን
የ አሁኑን እየረገምን
የነገዉን እየናፈቅን
የዛሬ ሰዉ መሆን አቅቶን
እድሜያችንን እንበላለን
እሸቱ ደምሴ
ሐምሌ 2000
The writter can be reached at admin@ethionation.com |